154802580
SBS Amharic - ኤስ.ቢ.ኤስ አማርኛ

Advertise on podcast: SBS Amharic - ኤስ.ቢ.ኤስ አማርኛ

Rating
★★★★★
4.5
from
20 reviews
This podcast has
1019 episodes
Language
English
Publisher
SBS
Explicit
No
Date created
2006/05/16
Latest episode
2026/10/15
Average duration
13 min.
Release period
1 days

Description

Independent news and stories from SBS Audio, connecting you to life in Australia and Amharic-speaking Australians. - ያልወገኑ ዜናዎችን ያቀርብልዎታል። ከአውስትራሊያ የሕይወት ታሪኮችና አማርኛ ተናጋሪ አውስትራሊያውያን ጋር ያገናኝዎታል።

Unlock SBS Amharic - ኤስ.ቢ.ኤስ አማርኛ podcast Email contact info,
Listeners & Audience details

Email contact information

Direct podcast contact details

Listeners

Audience numbers & engagement insights

Audience details

Podcast Insights

Social media

Check SBS Amharic - ኤስ.ቢ.ኤስ አማርኛ social media presence


Podcast episodes

Check latest episodes from SBS Amharic - ኤስ.ቢ.ኤስ አማርኛ podcast


የውይይት መድረክ፤ የኢትዮ-ኤርትራ ሉዓላዊነት፣ ብሔራዊ ጥቅምና የወደብ አጠቃቀም
2026/10/15
ወ/ሮ ሰብለወርቅ ታደስ (ኢትዮጵያዊት - አውስትራሊያዊት)፣ አቶ ልዑል ፍስሃ (ኢትዮጵያዊ - አውስትራሊያዊ)፣ እና አቶ ዮሐንስ ወንድማገኝ (ኤርትራዊ - አውስትራሊያዊ) የኢትዮጵያና ኤርትራን ብሔራዊ ጥቅም፣ ሉዓላዊነትና የግዛት አንድነት ማስከበርን በተመለከተ አተያዮቻቸውን ያንፀባርቃሉ። #sbsaudiopodcast
የውይይት መድረክ፤ የሰሜን ኢትዮጵያ ጦርነትና የኢትዮጵያ - ኤርትራ ወታደራዊ ውጥረት ማኅበረሰባዊ የሥነ ልቦና ጫና
2026/10/15
ወ/ሮ ሰብለወርቅ ታደስ (ኢትዮጵያዊት - አውስትራሊያዊት)፣ አቶ ልዑል ፍስሃ (ኢትዮጵያዊ - አውስትራሊያዊ)፣ እና አቶ ዮሐንስ ወንድማገኝ (ኤርትራዊ - አውስትራሊያዊ) በሰሜን ኢትዮጵያ ተከስቶ ባለው ጦርነት፤ እንዲሁም በኢትዮጵያና ኤርትራ መካከል ከርረው ያሉት ዲፕሎማሲያዊና ወታደራዊ ውጥረቶች በሀገረ አውስትራሊያ ነዋሪ በሆኑ ኢትዮጵያውንና ኤርትራውያን፤ ትውልደ - ኢትዮጵያውያንና ኤርትራውያን የማኅበረሰብ አባላት ላይ ስላሳደራቸውና ሊያሳድሯቸው ስለሚችሉት ስነ ልቦናዊ ተፅዕኖዎች ግለ አተያያቸውን ያጋራሉ። #sbsaudiopodcast
በርካታ አውስትራሊያውያን መንግሥት በቤት ኪራይ ክፍያ ጭማሪ ገደብ ላይ ጣልቃ ቢገባ እንደሚሹ ገለጡ
2026/10/14
በራፕ ኮከቡ ቱፓክ ሻኩር ግድያ የተከሰሰው ግለሰብ የ40 ዓመት እሥራት ተበየነበት #sbsaudiopodcast
የተባበሩት መንግሥትታ ድርጅት የሰሜን ኢትዮጵያ ጦርነት ዓለም አቀፋዊ ይዘት እንዳይኖረው ስጋት ያደረበት መሆኑን ገለጠ
2026/10/14
በኢትዮጵያ በዓመት 600 ቶን ወርቅ የማጣራት አቅም ያለው ፋብሪካ ተመረቀ #sbsaudiopodcast
ሕጎች እንዴት ነው የሚቀረፁት፤ እርስዎ ላይ ተፅዕኖ የሚያሳድሩትስ እንደምን ነው | አውስትራሊያ እንደምን እንደምትተገብር
2026/10/12
ሕጎች አውስትራሊያ ውስጥ የሚቀረፁት እንደምን ነው? በዉራንጄሪው አረጋዊ አጎት ዴቭ ዋንዲን አማካይነት የቢራራንግ እንዲሁም ያራ ወንዝ በመባል የሚታወቀውን ወንዝ ታሪክ ይቅሰሙ፤ እንደምን ፅንሰ ሃሳብ ለረቂቅ ድንጋጌነት እንደበቃ፤ በቪክቶሪያ ፓርላማ ይሁንታን እንዳገኘና ንጉሣዊ ፅድቅ ተችሮት ለሕግነት እንደበቃ። አውስትራሊያ እንደምን እንደምትተገበር እውነተኛ ታሪኮችን ነቅሶ፤ አውስትራሊያ ውስጥ መንግሥት እንደምን እንደሚሠራ፣ ሕጎች እንደምን እንደሚቀረፁና እንደሚሻሻሉ፣ እንደምን አተያዮን ማጋራት እንደሚችሉ ግንዛቤን የሚያስጨብጥዎ የSBS ፖድካስት ነው። ተከታትይ ክፍለ ዝግጅቶችንና አጭር ክፍለ ዝግጅቶችን በ60 ቋንቋዎች አውስትራሊያ እንደምን እንደምትተገብር ዋነኛ ገፅ ላይ አግኝተው ያድምጡ።
"የተባበሩት መንግሥታት ብዙውን ጊዜ ግጭት ማስቀረት ላይ ስኬታማ ሆኖ አላየውም፤ ግጭት ከተፈጠረ በኋላ ቶሎ ይገባል" ሌተና ጄኔራል ዮሐንስ ገብረመስቀል
2026/10/11
ሌተና ጄኔራል ዮሐንስ ገብረመስቀል፤ እ.አ.አ. ከ2012-14 በተባበሩት መንግሥታት ዋና ፀሐፊ ባን ኪሙን ለአቢዪ እንዲሁም ከ2014-16 ለደቡብ ሱዳን የተመድ ፀጥታ ኃይል አዛዥ ሆነው ተመድበው አገልግለዋል። በኢትዮጵያ ሀገር መከላከያ ሚኒስቴር ወታደራዊ መረጃ መምሪያ ዋና ኃላፊነት ሠርተዋል፤ በቅርቡም "የግጭት አዙሪት እና የአፍሪካ ቀንድ" በሚል ርዕስ መፅሐፍ ደርሰው ለአንባቢያን አበርክተዋል። ዳግም በተቀሰቀሰው የሰሜን ኢትዮጵያ ጦርነትና የኢትዮጵያና ኤርትራን ወታደራዊ የግጭት አቅጣጫ አንስተው የሙያና የተሞክሮ ግለ አተያያቸውን ያጋራሉ። #sbsaudiopodcast
"በኢትዮጵያና ኤርትራ መካከል ውጊያ መቀጠሉ የሚቀር አይመስለኝም፤ በማን የበላይነትና እንዴት ይቋጫል የሚለውን ወደፊት የምናየው ነው" ሌ/ጄኔራል ዮሐንስ
2026/10/11
ሌተና ጄኔራል ዮሐንስ ገብረመስቀል፤ እ.አ.አ. ከ2012-14 በተባበሩት መንግሥታት ዋና ፀሐፊ ባን ኪሙን ለአቢዪ እንዲሁም ከ2014-16 ለደቡብ ሱዳን የተመድ ፀጥታ ኃይል አዛዥ ሆነው ተመድበው አገልግለዋል። በኢትዮጵያ ሀገር መከላከያ ሚኒስቴር ወታደራዊ መረጃ መምሪያ ዋና ኃላፊነት ሠርተዋል፤ በቅርቡም "የግጭት አዙሪት እና የአፍሪካ ቀንድ" በሚል ርዕስ መፅሐፍ ደርሰው ለአንባቢያን አበርክተዋል። ዳግም በተቀሰቀሰው የሰሜን ኢትዮጵያ ጦርነትና የኢትዮጵያና ኤርትራን ወታደራዊ የግጭት አቅጣጫ አንስተው የሙያና የተሞክሮ ግለ አተያያቸውን ያጋራሉ። #sbsaudiopodcast
ርእሰ አድባራት ደብረሰላም መድሀኒአለም የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያ በአውስትራሊያ ያስገነባውን ሁለገብ ሕንጻ አስመረቀ
2026/10/10
ርእሰ አድባራት ደብረሰላም መድሀኒአለም የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያ በአውስትራሊያ ያስገነባውን ሁለገብ ሕንጻ በትናንትናው እለት አስመርቋል። የደብረሰላም ሜልበርን መድሃኒአለም ቤተክርስቲያን በአውስትራሊያ የመጀመሪያ እና በአባላት መጥንም ሆነ ባገልግሎት እየሰፋ በመሄዱ ፤ የአውስትራሊያና ኒውዝላንድ ሐገረ ስብከት ሊቀጳጳስ እንዲሁም የቅዱስ ሲኖዶስ አባል የሆኑት አቡነ ሉቃስ ከሀገር አሜሪካ " ርእሰ አድባራት ደብረሰላም መድሀኒአለም የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያ በአውስትራሊያ " እንዲባል ወስነዋል። መልእክታቸውም በብጹእ አቡነ ጴጥሮስ የኒውዬርክና አካባቢው ሊቀጳጳስና የቅዱስ ሲኖዶስ አባል በኩል ተላልፏል። በምረቃው ስነ ስርአት ላይ ብጹእ አቡነ ጴጥሮስ የኒውዬርክና አካባቢው ሊቀጳጳስና የቅዱስ ሲኖዶስ አባል፤ ብፁዕ አቡነ ዬሴፍ የሲዳማ ሐገረ ስብከት ሊቀጳጳስና የቅዱስ ሲኖዶስ አባል ፤ በአውስትራሊያና ኒውዝላድ ያሉ የየደብሩ አስተዳዳሪዎችና ምእመናን ፤ የግብጽ ኮፕት ቤተክርስቲያን አባቶች፤ የፓርላማ አባላት ፤ ሚኒስትሮች ፤ የአካባቢው ከንቲባዎች እና ካውንስለሮች ተገኝተዋል። #sbsaudiopodcast
በኢትዮጵያና ኤርትራ መካከል የቀጥታ ጦርነት ጅማሮ ስጋት ንሯል፤ በትግራይ የጦር ኃይሎች እንቅስቃሴ ቀጥሏል
2026/10/09
ኢትዮጵያ የኤርትራ ወታደሮች ከግዛቷ በአስቸኳይ እንዲወጡ ለተባበሩት መንግሥታት ድርጅት አመለከተች #sbsaudiopodcast
"ኢትዮጵያ በአድዋ ጦርነት በራሷ ምድር አጥቂ እንጂ ተከላካይ አልነበረችም" ዶ/ር ዳንኤል ካሳሁን
2026/10/06
ዶ/ር ዳንኤል ካሳሁን፤ በኦስቲን ኮሙዩኒቲ ኮሌጅ ጂ አይ ኤስ ተባባሪ ፕሮፌሰር፤ ሰሞኑን "ከፑንት እስከ 21ኛው ክፍለ ዘመን መጀመሪያ" በሚል ርዕስ በዶ/ር ግርማ አውግቸው አርታኢነትና በሴማዊ ጥናቶች መካነ ተቋም አሳታሚነት ለሕትመት በበቃው መፅሐፍ ላይ "የአድዋ ድልና ትርክት በጂኦግራፊያዊ ዕይታ ሲፈተሽ" በሚል ርዕሰ መጠሪያ ስላቀረቡት የመጣጥፋቸው ጭብጦች ይናገራሉ። #sbsaudiopodcast
ኢትዮጵያ በዓባይና በቀይ ባሕር ላይ ያላትን ጥቅም ዳግም አስገነዘበች፤ በትግራይ ውጊያው ቀጥሏል
2026/10/06
ዳግም በትረ ስልጣናቸውን የተረከቡት ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ በሰባተኛው የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የመመስረቻ ጉባኤ ላይ ባደረጉት ይፋ ንግግር፤ በቀጣዮቹ አምስት ዓመታት መንግሥታቸው ሁነኛ ትኩረት የሚሰጥባቸውን ዋነኛ አቅጣጫዎች አመላከቱ። #sbsaudiopodcast
Why power is split, and how that protects you | How Australia Works - ስልጣን ስለምን ነው የተከፋፈለው፤ እንደምንስ ነው ለእርስዎ ጥበቃ የሚያደርገው | አውስትራሊያ እንደም እንደም
2026/10/05
After receiving a fine for not wearing his motorbike helmet correctly, Hugo decides to have the matter heard in court. His story explains how Parliament, government and the courts have different roles, and how some official decisions can be questioned. - የሞተር ብስክሌት ሔልሜት በአግባቡ አላደረግክም በሚል አስባብ መቀጮ ሲደርሰው፤ ሁጉ ጉዳዩ ለችሎት ስሚ እንዲቀርብለት ከውሳኔ ላይ ደረሰ። የእሱ ታሪክ ፓርላማ፣ መንግሥትና ፍርድ ቤቶች ስላሏቸው የተለያዩ ሚናዎችና እንደምን የተወሰኑ ይፋ ውሳኔዎች ጥያቄ ሊቀርብባቸው እንደሚችል ግንዛቤ ያስጨብጣል። How Australia Works is an SBS podcast that uses real stories and clear explanations to help you understand how government work in Australia, how laws are made and changed, and how you can have a say. Listen to the series and find shorter versions in 60 languages on the How Australia Works main page. - አውስትራሊያ እንደምን እንደምትተገብር የ SBS ፖድካስት አውስትራሊያ ውስጥ የአውስትራሊያ መንግሥት እንደምን እንደሚንቀሳቀስ፣ ሕጎች እንደምን እንደሚቀረፁና እንደሚለወጡ፤ እርስዎም አተያይዎን እንደምን እንደሚያጋሩ እውነተኛ ታሪኮችን በመንቀስ ግንዛቤን እንዲጨብጡ የሚያግዝዎ ነው። ተከታታይ ክፍለ ዝግጅቶቹን ያድምጡ፤ ቅንጭብ ዝግጅቶቹንም በ60 ቋንቋዎች አውስትራሊያ እንደምን እንደምተገብር ዋነኛ ገፅ ላይ ያግኙ።
የኢትዮጵያ መከላከያ ሠራዊትና አጋሮቹ መቀሌን መቆጣጠር
2026/10/05
በኢትዮጵያና ኤርትራ መካከል እየበረታ ያለው ግጭት ያሳሰባት ዩናይትድ ስቴትስ ሁለቱ ሀገራት ከግጭት ተቆጥበው ወደ ንግግር እንዲመለሱ አሳሰበች #sbsaudiopodcast
የአውስትራሊያ መንግሥት የከሰል ማዕድን ቁፋሮ ማስፋፋት በቅድመ COP31 ጉባኤ ተቃውሞ እየጠበቀው ነው
2026/10/05
አውስትራሊያ ራሷን በሰከነ የምጣኔ ሃብት ሀገርነት፣ የሰው ሠራሽ አስተውሎት ዘርፍ መሪነትና የታዳሽ ኃይል ማዕከልነት ለማስተዋወቅ ወጥናለች #sbsaudiopodcast
የአውስትራሊያ የቋንቋ ለውጥ የአዲሱ የSBS ክለሳ ቀራጭ ይሆናል
2026/10/04
በርካታ ከአንድ ቋንቋ በላይ ተናጋር የሆኑ ፍልሰተኛ ቤተሰቦች የSBS ሬዲዮ የተለያዩ ቋንቋ ፕሮግራሞችን ከማድመጥ የተያያዙ የግል ትዝታዎችና ልዩ ትስስሮሽ አሏቸው። እነዚህ ፕሮግራሞች ባለፉት ዓመታት ተለውጠዋል፤ ተስፋፍተዋል። እናም አሁን SBS በዘመናዊቷ አውስትራሊያ የሚታዩትን የማኅበረሰብ ለውጦችና ፍላጎቶችን ለማንፀባረቅ የቋንቋ አገልግሎቶቹን ክለሳ ለማካሄድ በመሰናዶ ላይ ይገኛል። ለክለሳውም የሕዝባዊ ምክክር ጊዜ ይኖራል። ይህም ከመስከረም 25 እስከ ጥቅምት 3 ድረስ ይከናወናል። #sbsaudiopodcast

Podcast reviews

Read SBS Amharic - ኤስ.ቢ.ኤስ አማርኛ podcast reviews


4.5 out of 5
20 reviews
★★★★☆
G Wubetu 2021/12/13
Ethiopian
Thank you for presenting diverse people and ideas. What makes it more appealing is the program is presented by people who knows the country, history a...
★★★★★
TØMA5 2016/07/15
Muchas Gracias!!!
I'm from Ethiopia and I'm so thankful to find this! 🇪🇹✌🏾✌🏿
★★★★★
Dawit Agonafer 2014/12/21
Thank you
Dear Kassahun, Thank you for the informative, timely and thought provoking programs you put together. Your fairness and respectful way you engage you...
check all reviews on apple podcasts

Podcast sponsorship advertising

Start advertising on SBS Amharic - ኤስ.ቢ.ኤስ አማርኛ relevant audience podcasts


What do you want to promote?